የኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ

የኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ

Tuesday, September 8, 2015

ነሐሴ 27፣2007
በ2ኛው የዓለም ጦርነት ዘመን የጀርመን ናዚዎች ፣ የጃፖን ሚሊተሪስቶችና የጣሊያን ፋሽስቶች ዓለምን የመቆጣጠር ክፉ ሃሳብና ምኞት ባደረባቸው ጊዜ የጥፋት ቁርኝት ፈጠሩ፡፡ “የአክሲስ” ኃይሎች ተብለው ተጠሩ፡፡ ክፉ ምኞታቸው እንደ ጉም በነነ፡፡ ከአክሲሶቹ የመጨረሻዋ ተሸናፊ የሆነችው ጃፖን እጅ የሰጠችው የዛሬ 70 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡ በ2ኛው የዓለም ጦርነት የአውሮፖ የጦርነቱ ቆስቋሾች የጣሊያን ፋሽስቶችና ዋነኛዋቹ ዘዋሪዎች የጀርመን ናዚዎች ተከታትለው ተሸነፉ፡፡ የሃፍረት ሸማም ተከናነቡ፡፡ የኢስያ የአክሲስ አጋር የሆነችው ጃፖንም ከጥቂት ወራት በኋላ ከዚህ ሽንፈት ማምለጥ አልቻለችም፡፡ ወደ ጦርነቱ ማብቂያ ጃፖን ጭንቅ ጥብ ላይ ወደቀች፡፡ ግዙፍ የባሕር ኃይሏ እንደ ቀድሞው የጦር አቅሙን ማሳየት በማይችልበት ሁኔታ ተሽመደመደ፡፡ በኢሲያ አህጉርና በፖስፊክ ቀጠና ተቆጣጥራቸው የነበሩ መሬቶችንና የደሴት አካላትን ሁሉ በህብረቱ ኃይሎች ተቀማች፡፡

No comments :

Post a Comment

Qedamawi Haile Selassie

Qedamawi Haile Selassie
This then is the ultimate challenge. Where are we to look for our survival, or the answers to questions which have never before been posed?