ቡና የተክል አይነትና ከዚህ ተክል ቡን የሚባል መጠጥ የሚወጣው ነው። መጀመርያ የታወቀው በኢትዮጵያ ሲሆን ምናልባት በዚህ የተነሳ ቡና በተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ከፋ ከሚለው ስም ጋር ተቀራራቢ የሆነ ስሞች ተስጥተውት ይገኛል (ለምሳሌ እንግሊዝኛ፦ coffee /ኮፊ/ በፈረንሳይኛ ካፌ (café)በዳች ኮፊ (koffie) በእብራይስጥኛ ካፈ (ka-feh) በስዊድንኛ ካፈ (kaffe) ወዘተ ) ምናልባት ከድሮው የከፋ መንግሥት በተዛመደ መልኩ ሊሆን ይችላል። በአንድ ትውፊት መሠረት በመጀመርያ ያገኘው ሰው ካልዲ የተባለ አንድ ኢትዮጵያዊ እረኛ ፍየሎቹ ፍሬውን በልተው ሲጨፍሩ ስለተመለከተ ነበር።
የቡና የስነ ፍጥረት ስሙ Coffea arabica (ኮፊ ኣራቢካ) ሲሆን የዚህ የኢትዮጵያ ቡና ዘር በጣዕሙ ጥሩነት የተነሳ በጣም ተወዳጅ ነው።
No comments :
Post a Comment