--የኢትዮጲያ የንግድ ጽህፈት ቤት ታሪክ--
ድንገት እግር ጥሎኝ የኢትዮጲያ የንግድ ሚንስቴር ድረ ገጽ ውስጥ ገብቼ ገጽ ሳገላብጥ ያጋጠመኝ እና እጅግ በጣም ያሰዘነኝ ነገር ቢኖር የኢትዮጲያ የንግድ ጽህፈት ቤት ከ122 ዓመት በላይ የሆነ ረጅም እና አስገራሚ አስተዋጾ ቢኖረውም ግን በዚህ ድረ ገጽ ላይ ታሪኩ የተጻፈው በውሮጳ አቆጣጠር ከ1995 ዓ ም ጀምሮ ያለው ብቻ ነው።
ድረ ገጹን ያቋቋሙት ሰውች ታሪኩን ሳያውቁት ቀርተው ነው? ከሆነ ርግብ በአንድ ክንፍ እንዳማትበረው ሁሉ ከመሰረቱ ሳይነሱ የተቆራረጠ ታሪክ ይዘው ንግድ ምኒስቴርን የሚያክል አንድን አገር በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያገለግል ትልቅ ጽህፈት ቤት የሚወክል ድረ ገጽ መክፈቱ ደግ አይደለም። ወይስ ይህ ድርጊት ሆን ተብሎ የታሰበ ታሪክ የማጥፋት ዘመቻ ይሆን?
...

በስዊዝ ተወላጅ አማካሪያቸው በቢተወደድ አልፍረድ ኢልግ አማካኝነት የኢትዮጲያን ንግድ ጽህፈት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የጥንቷ ግንፍሌ መንደር አካባቢ በውሮጳ አቆጣጠር በ1893 ዓም ላይ ያቋቋሙት ዝነኛው የክፍለ ዘመኑ ድንቅ ክስተት አጤ ምንሊክ ናቸው። ስለስልጣኔ ካወራን ወደድንም ጠላንም የእሳቸው ስም በጉልህ መጠራት አለበት።
በዚህ ዘመን የነበሩት የመጀመሪያው የዘመናዊ ንግድ ሚኒስቴር ወይም ነጋድራስ ( የነጋዴ ራስ) ፊት አውራሪ ቢተወደድ ኃይለ/ ጊዎርጊስ ወልደ ሚካኤል ይባላሉ። አባ ድፋው የተባለውን የጦር ስም የተሰየሙት አደዋ ዘምተው በፈጸሙት ጀብዱ ነው እንጂ ዋና መጠሪያ ስማቸው ግን አይደለም።
በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1954 ዓም አካባቢ የሐረሩ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በምስሉ ላይ እንደሚታየው ትልቅ ህንጻ ገንብተው የንግድ ጽህፈት ቤቱን ዘመኑን በሚመጥን አይነት መንገድ አሻሽለው እንደገና ለአገልግሎት አቆረቡት።
ከብዙ በከፊል እውነተኛው የኢትዮጲያ የንግድ ሚኒስቴር አመጣጥ እና አገልግሎት ታሪክ ይህ ነው።

No comments :
Post a Comment